በኢትዮጵያ የሚታዩት ግጭቶች እና የግብአቶች እጥረት፣ የወባ በሽታን ለመከላከል ፈተና መደቀናቸውን፣ የክልሎች የጤና ቢሮዎች አስታወቁ፡፡
የዐማራ፣ የኦሮሚያ እና የትግራይ ክልሎች የጤና ቢሮዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ በክልሎቹ የሚታየው የወባ በሽታ ስርጭት "አሳሳቢ" ኾኗል፡፡ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ እንደ አጎበር እና ኬሚካል ያሉ ግብአቶች እጥረትም እንዳለ የጠቆሙት ቢሮዎቹ፣ በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ግጭቶች ደግሞ የወባ መከላከያ ግብአቶችን ለማሰራጨት "ዕንቅፋት ኾነዋል፤" ይላሉ።
የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ፣ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ፣ በኢትዮጵያ 8ነጥብ4 ሚሊዮን ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም