በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሔራዊ ባንክ ለኤም-ፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠ


ብሔራዊ ባንክ ለኤም-ፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

ብሔራዊ ባንክ ለኤም-ፔሳ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠ

ብሔራዊ ባንክ፣ የሳፋሪኮም አካል ለኾነውና ኤም-ፔሳ ለተባለው ኩባንያ፣ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የክፍያ እና ሒሳብ ማወራረጃ ሥርዐት ተጠባባቂ ዲሬክተር የኾኑት አቶ ሰሎሞን ዳምጠው፣ በጉዳዩ ዙርያ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ ለኤም-ፔሳ

ኩባንያ፣ የሞባይል ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት፣ የክፍያ ዐዋጅ ማሻሻያ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ኩባንያው፣ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የተሠማራ የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስተር ሲኾን፣ በዘርፉ ስለሚኖረው ተጽእኖ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት የፋይናንስ ባለሞያ አቶ ጋሻው ደሳለኝ፣ ኤም-ፔሳ ባለው ትልቅ ዐቅም እና ልምድ፣ ለደንበኞች ልዩ ልዩ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ አመልክተዋል፡፡

ኾኖም ብሔራዊ ባንክ፣ እንደ ኤምፔሳ ያሉትን የውጭ ተዋናዮችንና ባንኮችን ለመቆጣጠር ዐቅሙን መገንባት እንዳለበት የፋይናንስ ባለሞያው ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

XS
SM
MD
LG