አምስት ሚሊዮን መቀመጫዎች ለውድድር የሚቀርቡበት ይህ የአካባቢ ምርጫ፤ በተለይ በተቃዋሚዎች ዘንድ ቅሬታን ሲያስከትል ቆይቷል።
የምክር ቤት አባላት ቁጥር እንዲጨምርና በድምሩ አምስት ሚሊዮን እንዲደርስ የተደረገው የተቃዋሚዎችን የማሸነፍ ዕድል ለማጥበብ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። ምርጫ ቦርድ በዚህ አይስማማም።
ለወረዳና ለቀበሌ፣ በአንዳንድ ክልሎች ደግሞ ለዞን ምክር ቤቶች የሚደረጉ ምርጫዎች በዚሁ ምርጫ ሥር ይከተታሉ፡፡ በአዲስ አበባ ደግሞ ምርጫው በክልሉ መስተዳድር ሥር ይካሄዳል፡፡
138 መቀመጫዎች ላሉት የአዲስ አበባ ምክር ቴት የሚካሄደው ምርጫ ለወትሮ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማለትም ከፌደራሉ ፓርላማ ምርጫ ጋር በተመሣሣይ ወቅት የሚካሄድ ቢሆንም ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ግን የጊዜ ሠሌዳው ተዛብቷል፡፡
በዚያ ምርጫ ሁሉንም መቀመጫዎች አሸንፎ የነበረው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በወቅቱ በነበሩ የፖለቲካ ምክንያቶች አስተዳደሩን እንዲረከብ ባለመደረጉ ከተማዋ ለአጭር ጊዜ በባለአደራ አስተዳደር ሥር መቆየቷ፣ በኋላም ሌላ ምርጫ ማካሄዷ ይታወሣል፡፡
በዚህም ምክንያት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ በመላ ሃገሪቱ ከሚካሄዱ የአካባቢ ምርጫዎች ጋር ይካሄዳል፡፡
በሚቀጥለው ዓመት ለሚካሄዱት ለእነዚሁ ምርጫዎች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ፍቃደ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ፡፡