በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማኅበራዊ ሚዲያ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መቆጣጠሪያ ሕጎች ተፈጻሚነት ምን ያህል ነው?


በማኅበራዊ ሚዲያ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መቆጣጠሪያ ሕጎች ተፈጻሚነት ምን ያህል ነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:03 0:00

በማኅበራዊ ሚዲያ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መቆጣጠሪያ ሕጎች ተፈጻሚነት ምን ያህል ነው?

ኢትዮጵያ፣ በማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ጨምሮ በኢንተርኔት አማካይነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል፣ ከፍትሐ ብሔር እና ከወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ድንጋጌዎች በተጨማሪ፣ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ዐዋጅ እንዲሁም የኮምፒዩተር ወንጀል ዐዋጅ የመሳሰሉትን አጽድቃለች።

ኾኖም፣ በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ምኅዳር ውስጥ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች፣ የጥላቻ ንግግሮች እና ሌሎች ወንጀሎች እየጨመሩ መሔዳቸውን በርካታ ተንታኞች ያመለክታሉ፡፡ ዐዋጆቹም ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ እና መረጃ የማግኘት መብትን ከመጋፋት ውጭ፣ የኅብረተሰቡን ደኅንነት መጠበቅ እንዳልቻሉ ይከራከራሉ።

ለመኾኑ፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የስም ማጥፋት፣ የግለኝነት መብትን መጋፋትና ሌሎች ከሥነ ምግባር ያፈነገጡ መረጃዎች ስርጭት የመሳሰሉ ወንጀሎችን የሚፈጽሙ፣ ወደ ሕግ የሚቀርቡባቸው ማኅቀፎች ምንድን ናቸው?

የኅብረተሰቡን ደኅንነት ለመጠበቅ ያላቸው ዐቅምስ ምን ይመስላል? ስትል፣ ዘጋቢያችን የሕግ ባለሞያ እና ፌደራል ፖሊስን አናግራ ተከታዩን አሰናድታለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG