በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሲዳማ የደርሰው አደጋ እንዳይደገም ስጋት እንዳላቸው ተወላጆቹ ገለፁ


በሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ሐሊላ መሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በሚገኙ ሦስት መንደሮች በዝናብ ምክኒያት በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተጎዱ ሰዎችን ለማውጣት ሲሞክሩ
በሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ሐሊላ መሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በሚገኙ ሦስት መንደሮች በዝናብ ምክኒያት በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተጎዱ ሰዎችን ለማውጣት ሲሞክሩ

በሲዳማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተረፉ ሰዎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል ሲሉ በውጭ የሚገኘው የሲዳማ ተወላጆች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

በሲዳማ የደርሰው አደጋ እንዳይደገም ስጋት እንዳላቸው ተወላጆቹ ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:33 0:00

በሲዳማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተረፉ ሰዎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል ሲል በውጭ የሚገኘው የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክሪያቲክ ንቅናቄ አስታወቀ።

የአካባቢው ተወላጅ የሆኑና የሲዳማ ዜና መረብ የሚል የኢንተርኔት ድረገፅ ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች በበኩላቸው አካባቢው የተዘነጋ መሆኑን ጠቅሰው የአካባቢው አስተዳደር ለማኅበረሰቡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ሐሊላ መሎ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በሚገኙ ሐሊላ መሎ፣ ፍንጭ ውሃና ወሸረቤ በተበሉ መንደሮች በደረሰ የመሬት መንሸራተት ዐስራ ስድስት ሴቶችና ስምንት ወንዶች በድምሩ 23 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን በትናንተናው ምሽት መዘገባችን ይታወሳል።

በተጨማሪም በጋሞ ጎፋ ዞን ዳራ ማሎ ወረዳ በጮዬ በተባለ አካባቢ በከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውና 17 ሰዎች መጎዳቻቸውን መዘገባችን ይታወሳል። እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች አካባቢው የተዘነጋ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋ ሲመጣ በቀላሉ የሰዎችን ሕይወት ይቀጥፋል ይላሉ።

በሐዋሳ ዩንቨርስቲ የሲቪክ እና የፍልስፍና መምሕር የነበረውና አሁን የሲዳማ የዜና መረብ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የአካባቢውን ሁኔታ የሚከታተለው አቶ ያሬድ እስጢፋኖስና የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክሪያቲክ ንቅናቄ መስራች አቶ በቀለ ዋዩን ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG