በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ ክብሮም በርኸ በዋስ ከእስር ተለቀቁ


ፎቶ ፋይል፦ አቶ ክብሮም በርኸ
ፎቶ ፋይል፦ አቶ ክብሮም በርኸ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቶ ክብሮም በርኸ በዋስ እንዲፈቱ በመወሰኑ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ፡፡

የባይቶና ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክብሮም በርኸ በዋስ እንዲወጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የወሰነው ባለፈው ዓርብ ዕለት ሲሆን በዛሬው ዕለት የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ተፈፃሚ ሆኖ አቶ ክብሮም በርኸ ከእስር ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

ቀደም ሲል ዐቃቤ ህግ በአቶ ክብሮም በርኸ ላይ ክስ እንዲመሰርት በፍርድ ቤት የ10 ቀን ቀጠሮ ሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ ዓርብ ዕለት በነበረው ውሎ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶ መቅረብ እንዳልቻለ ጠበቃው አቶ ወንደሰን በፍቃዱ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡ በፖሊስ የተጠየቀው የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜም ፍርድ ቤት አልተቀበለውም፡፡

አቶ ክብሮም በርኸ እና ከሳቸው ጋር የተያዙ አራት ሰዎች በፌዴራሉ መንግሥት በሽብርተኝነት ለተፈረጀው ህወሓት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እና በማህበራዊ ሚዲያ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን በማሰራጨት ወንጀል ተጠርጥረው፣ ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን

ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት መታየት የጀመረው ነሐሴ 25 ቀን ነበር፡፡

አቶ ክብሮም በርኸ ሐምሌ 5 ቀን የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋስ እንዲወጡ ከወሰነላቸው በኋላ ከእስር ሳይለቀቁ ወደ አልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን እና ከ35 ቀናት በኋላ ወደ አዲስ አበባ አባሳሙኤል ማረሚያ ቤት መምጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG