በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ኬንያ በከፍተኛ ደረጃ ለመተባበር የጋር ኮሚሽን መሰረቱ

ኢትዮጵያና ኬንያ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ልዩ ቦታ የሚሰጠው ሥምምነት ፍጥነት ባለው መልክ ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምተዋል። ይህ ስምምነት ለዜጎቻቸው የኢኮኖሚና የፀጥታ ደኅንነት ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ይታመናል።

ኢትዮጵያና ኬንያ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ልዩ ቦታ የሚሰጠው ሥምምነት ፍጥነት ባለው መልክ ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምተዋል። ይህ ስምምነት ለዜጎቻቸው የኢኮኖሚና የፀጥታ ደኅንነት ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ይታመናል።

ኢትዮጵያና ኬንያ በከፍተኛ ደረጃ ለመተባበር የሚያስችላቸው የጋር ኮሚሽን መስርተዋል። በኢትዮጵያ ከተማ ሞያሌ ላይ አንድ የድንበር ጣብያ መመስረቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የሰዎችና የዕቃዎች ዝውውር እንዲሻሻል አድርጓል።

ይሁንና የሁለቱም ሀገሮች ህዝቦች ከዚህ ከልዩው ግንኙነት ለመጠቀም እንዲችሉ ግልጽ የጊዜና የማዳረስ መስመር እንዲኖር ያስፈልጋል ሲሉ የኬንያው ፕሬዚዳንት እሁሩ ኬንያታ አስገንዝበዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የኢትዮጵያው ጠቃላይ ሚኒስተር አብይ አሕመድ ኬንያን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ሁለቱ መሪዎች ሃገሮቻቸው ስለትሰማሙበት የመብራት ሀይል ግዢ ጉዳይ ተግባራዊ ስለማደረግ እንደተናጋገሩ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG