ሀዋሳ —
ኢትዮጵያ በደቡብ ኦሞ ዞን ያንጋቶም ወረዳ በቱርካና በኩል ከኬንያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የፀጥታ ኃይል እንደምታሰፍር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ተናገሩ።
ይህንን የርዕሰ መስተዳደሩን ንግግር ጠቅሰው ምክንያቱን ለአሜሪካ ድምጽ ያብራሩት የክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን ከኬንያ በቱርካና በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ በደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ አርብቶ አደሮች ላይ ታጣቂዎች የሚፈጽሙባቸውን ጥቃት ለመከላከል እንደሆነ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።