WASHINGTON DC —
ከአንድ ዓመት በላይ በእስር የቆዩት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች በዛሬወእለት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ፊት ቀርበዋል። አቃቤ ሕግ ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በያዘዉ ቀጠሮ መሰረት ቀሩኝ ካላቸዉ 13 ምስክሮች ዉስጥ ሶስቱን ማቅረቡን የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። ምስክሮቹ እንደቀድሞዎቹ ሁሉ ተከሳሾቹ ከተያዙባቸዉ ቦታዎች ሞባይል፣ ላፕ ቶፕ እና ሲዲ መያዙን አይተናል ማለታቸዉን ጠበቃዉ አስረድተዋል።
ከአንድ ወር ተኩል በፊት በዋለዉ ችሎት አቃቤ ሕጉ ምስክሮችን ለመስማት የተሰጠዉ ጊዜ አጭር መሆኑን፣ ለማስረጃነት ሊቀርቡ የነበሩትን ሲዲዎች የያዙት ግለሰብ ከአገር ዉጭ መሆናቸዉን እንዲሁም በእግዚቢትነት የያዛቸዉን ሞባይል ስልኮችና ላፕ ቶፖችን ለማቅረብ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠዉ መጠየቁ ይታወቃል።
የዛሬዉን የችሎት ዉሎ በተመለከተ መለስካቸዉ አመሃ አቶ አመሃ መኮንንን አነጋግሯቸዋል።