በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነፃ የእሥልምና ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ነው ተባለ


ትክክለኛ አመራር ለሚሰጥ የሃማኖት ተቋም ምሥረታ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮችም እንዲተባበሩ ጥሪ ተደረገ፡

በኢትዮጵያ እሥልምና ዙሪያ የሚነሱ አነጋጋሪ ጥያቄዎች የመፍትሔ ሃሳብ የሰጡ ሁለት ምሁራን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አመራር የሚሰጥ የሃይማኖት ተቋም ማቋቋም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖቱ ዙሪያ ለሚካሄደው ውዝግብ ዓይነተኛ መፍትሔ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የባህል ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አህመድ ዘካሪያ፤ በእሥልምና ጉዳዮች ዙሪያ ብዙ መፅሐፎችን የፃፉና ብዙዎችንም የተረጎሙ አቶ ሐሰን ታጁ በኢትዮጵያ የእሥልምናን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ታሪክ፣ በወቅቱ በሃይማኖቱ ዙሪያ ውዝግብ የሚሰማበትን ምክንያትና የመፍትሔ ሃሳብ በየበኩላቸው ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ አስተያየት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እስከ 1974 ዓ.ም በአንድ ሃይማኖት የበላይነት የሚያምንና ሌሎቹን በመጨፈለቅ፣ በተለይም እሥልምናን በመምታት ላይ የተመሠረተና ድጋፍ ያገኝ የነበረውም ከቤተክህነት እንደነበር ተናግረዋል።

የሙስሊሞችና የክርስትና እምነት ተከታዮች ማህበራዊ ግንኙነት ግን ከፓለቲካው በጣም የተሻለና ተሳስቦ የመኖርን ታሪክ የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልፀዋል።

አሁን በኢትዮጵያ እሥልምና ዙሪያ ለተከሰቱ ጥያቄዎችና ውጥረቶች ምሁራኑ ከኅብረተሰባዊነት (ሶሻሊዝም) ርዕዮተ-ዓለም መውደቅ በኋላ በዓለም ዙሪያ የህዝቦችን ወደ ሃይማኖት መመለስ አዝማሚያ፣ የኢንተርኔትና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን መስፋፋት ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን እንዲያዳብሩ ማስቻሉን አመልክተዋል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከሁለቱ ምሁራን ጋር የተደረገውን ሰፋ ያለ ውይይት እንድታዳምጡ እንጋብዛለን።

XS
SM
MD
LG