በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እሥልምና በኢትዮጵያና የሰሞኑ ውዝግብ


በሰሞኑ የኢትዮጵያ የእሥልምና አስተሣሰቦች፣ ንግግሮችና ውዝግቦች እንዲሁም በአወሊያ ትምህርት ቤት ዙሪያ የሃይማኖቱ ምሁራን ለአድማጮች ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፡፡

በቅርቡ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሙስሊም ትምህርት ቤት አወሊያን ያስተዳድር የነበረው ድርጅት አክራሪነትንና ጥላቻን ያስተምር ስለነበር እንዲባረር ተደርጓል ማለታቸውና በአወሊያ ጉዳዮች ዙሪያ የተቋቋመው ኮሚቴ ተጠሪ ደግሞ ሚኒስትሩ ለተናገሩት ማስረጃ የለም ማለታቸውን ዘግበናል።

መንግሥት አህባሽ የተባለው የእስልምና ዘርፍ ትምህርት ላይ እንዲውል እያደረገ ነው፤ ይህን የሚደግፉና የሚነቅፉ የሃይማኖቱ ተከታዮች አሉ።

ለምን? አህባሽ ቀድሞ አብዛኛው ህዝበ ሙስሊም ከሚከተለው ዕምነት በምን ይለያል? ወሃቢያ የሚባለውስ የዕምነት ዘርፍ ምንድነው? እነዚህና ሌሎችም ተዛማጅ ጥያቄዎችን አድማጮች ለሃይማኖቱ ምሁራን አንስተዋል፡፡

በጥያቄዎ መልስ ዝግጅት ቀርበው መልስ ለአድማጮች ጥያቄዎች መልስ የሰጡልን አቶ አደም ከሚል ከኢትዮጵያ፣ ኢማም ሼህ ሣላህዲን ከአትላንታ - ዩናይትድ ስቴትስ ናቸው፡፡

ቅንብሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG