በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚያዝያ የምግብ ዋጋ በ32ከመቶ ጨመረ


የእህል ዋጋ በክረምት ወቅት እንደሚወደድ ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል
የእህል ዋጋ በክረምት ወቅት እንደሚወደድ ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል

በክረምት ወቅት የእህል ዋጋን በእጅጉ እንደሚወደድ ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል

በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበቱ በእጅጉ ተባብሷል። የኢትዮጵያ መንግስት የመረጃ ምንጭ የሆነው የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በዛሬውለት ይፋ ባደረገው የአጠቃላይ ኢኮኖሚ መረጃ ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ከነበረው የዋጋ ሁኔታ በዚህ አመት የ29.5 ከመቶ የዋጋ ንረት ተከስቷል።

ይሄ ከፍተኛ የዋጋ መወደድ ባለፈው የመጋቢት ወር ከነበረው የ25 ከመቶና በየካቲት ወር ከነበረው የ19 ከመቶ እድገት የበለጠ ሆኗል።

የዋጋ ግሽበቱ የተከሰተው በዋነኝነት በምግብ ዋጋ ላይ በታየው ጭማሪ መሆኑን የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ያትታል። በምግብ ዋጋ ላይ የ32.5 ከመቶ ጭማሪ ታይቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት የብር ምንዛሬን በነሐሴ ወር ወደ ሀያ ከመቶ የሚጠጋ ማስተካከያ ካደረገና አከታትሎም በጥር ወር የዋጋ ጣራ ካወጣ ወዲህ፤ በአቅርቦትና ፍላጎት ከፍተኛ አለመመጣጠንም በመታየቱ፤ ኑሮ አልቀመስ ብሏል። ግሽበቱን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ዶ.ር ወልዳይ አምሃ የሚከተለውን ማብራሪያ ይሰጣሉ።

ውይይቱን ያዳምጡ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG