በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ የምታደርገውን ጥቃት አባብሳ ቀጥላለች” ሂውማን ራይትስ ዋች


የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ የሚያደርገውን ጥቃት አባብሶ ቀጥሏል ሲል ዛሬ አስታውቋል።

ባለፈው ታኅሳስ አምስት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ማለትም በሃገሪቱ ለረጅም ጊዜ ያገለገለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ማኅበር ባለፈው ታኅሣሥ መታገዳቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አውግዟል።

ድርጅቶቹ የታገዱት “ገለልተኝነት ይጎድላቸዋል፣ እንዲሁም ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ነበር።

የመንግሥት ድርጊት “እየተባባሰ ያለውና በሲቪል ማኅበረሰቡ ላይ የሚደረገው ጥቃት ነው” ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች አክሏል።

“የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በሰብአዊ መብት ቡድኖች ላይ የጥቃት ዘመቻ ከፍተዋል” ሲሉ የቡድኑ የአፍሪካ ዲሬክተር ማዉሲ ሴጉን ተናግረዋል።

“በሰብአዊ መብቶች ላይ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን የሚሰንዱና ሰብአዊ መብቶችን የሚያራምዱ ቡድኖችን በማገድ መንግሥት ገለልተኛ የሆኑ ወገኖችን ክትትል እንደማይታገስ አሳይቷል” ሲሉም አክለዋል።

የጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ ቃል አቀባይ የሆኑት ቢልለኔ ስዩም በበኩላቸው፣ መንግሥት ሁሉንም ካላት የሚያሳትፍ አካታችና ህጋዊ ምህዳርን ፈጥሯል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG