በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የተፈናቃዮች ተቋም አለመኖሩ በጥበቃቸው ላይ ክፍተት ፈጥሯል” ኢሰመኮ


“የተፈናቃዮች ተቋም አለመኖሩ በጥበቃቸው ላይ ክፍተት ፈጥሯል” ኢሰመኮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

“የተፈናቃዮች ተቋም አለመኖሩ በጥበቃቸው ላይ ክፍተት ፈጥሯል” ኢሰመኮ

በኢትዮጵያ የተፈናቃዮችን ጉዳይ የሚከታተል ራሱን የቻለ ተቋም እና ብሔራዊ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ላይ ክፍተት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ፡፡

በኮሚሽኑ የስደተኞች፣ ተፈናቃዮችና ፍልሰተኞች መብቶች ተጠባባቂ ዳይሬክተር እንጉዳይ መስቀሌ እንደተናገሩት፣ ኮሚሽኑ የ2014 ዓ.ም የተፈናቃዮች ጥበቃን በሚመለከት ባደረገው ክትትል፣ የህግ ማዕቀፍና ተቋማዊ መዋቅር አለመኖር በተፈናቃዮች ጥበቃ ላይ ክፍተት የፈጠሩ ሁለት ቁልፍ ጉዳዮች እንደነበሩ ለይቷል፡፡

በዓመቱ የነበረውን የተፈናቃዮች ሁኔታ በማስመልከት አስተያየት የሰጡት የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሑሴን በበኩላቸው፣ “የህግ ማዕቀፍና የተቋማዊ አደረጃጀት ክፍተቶች በዓመቱ ለታዩት ችግሮች አስተዋፀዖ ቢያደርጉም፣ ብቻቸውን መፍትሔ ያመጡ ነበር ብዬ ግን አላምንም” ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል መንግሥት ኃላፊዎች አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG