በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሂዩማን ራይትስ ዋችን ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ


 የሂዩማን ራይትስ ዋችን ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:01 0:00

የሂዩማን ራይትስ ዋችን ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ

ምዕራብ ትግራይ ውስጥ “በዐማራ ኃይሎችና በአካባቢ ባለሥልጣናት ዘር ማፅዳት ተፈፅሟል” ሲል ሂዩማን ራይትስ ዋች ያሰማውን ክሥ የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ዛሬ ባወጣው ምላሽ የያዘ መግለጫ የሂውማን ራይትስ ዋችን ሪፖርት “መሠረተ ቢስ” ብሎታል።

“ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው ድርጅት እ.ኤ.አ. ጁን 1 / 2023 (በኢትዮጵያ ቀመር ግንቦት 24 / 2015 ዓ.ም መሆኑ ነው) በሃገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የሚገልፅ መሠረተ ቢስ ሪፖርት አውጥቷል” ይላል የመንግሥቱ ምላሽ።

ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሐሙስ ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ህወሃት ፕሪቶርያ ላይ የሰላም ስምምነት ከፈረሙ ሰባት ወራት ቢቆጠሩም “በአዛጋቢው ወልቃይት እና በሑመራ አካባቢዎች ዘር የማፅዳት ዘመቻ እየተካሄደ ነው” ሲል ከሥሶ ነበር፡፡

ቡድኑ በዚያ ሪፖርቱ “የዐማራ ኃይሎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት የትግራይ ተወላጆችን በኃይል ማፈናቀላቸውን ቀጥለዋል” ይልና “አድራጎቱን በመፈፀም ላይ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎችን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያግድ፣ እንዲመረመርና በአግባቡ እንዲቀጣ” ሲል ጥሪ አቅርቦ ነበር፡፡

የመንግስት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት በዛሬው ምላሹ “በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ብሏል።

የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ለማለት የቀረበው ሪፖርት ይዘት ሲታይም ተገቢው ምርመራ ያልተደረገበትና በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ከመሆኑ አንፃር እምነት የሚጣልበት አይደለም”

“የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ለማለት የቀረበው ሪፖርት ይዘት ሲታይም ተገቢው ምርመራ ያልተደረገበትና በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ከመሆኑ አንፃር እምነት የሚጣልበት አይደለም” ሲል አክሏል።

ይኸው የመንግሥቱ ምላሽ አክሎ ባስተላለፈው መልዕክት “የሽግግር ፍትህ ሂደቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በፈፀሙ ወገኖች ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነትን ማስፈንን ጨምሮ እውነትን የማፈላለግና ተጎጂዎችንም መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ማዕቀፍ ይፈጥራል፤ በተጓዳኝ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሀገራችን የሚታዩ ግጭትና አለመግባባቶችን ከሥር መሠረታቸው በመለየት በዘላቂነት ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል” ብሏል።

XS
SM
MD
LG