በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ሪፖርት


ኃይለማርያም ደሣለኝ - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር /ፎቶ - ፋይል/
ኃይለማርያም ደሣለኝ - የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር /ፎቶ - ፋይል/
የኢትዮጵያ ፓርላማ
የኢትዮጵያ ፓርላማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት በተያዘው የበጀት ዓመት በ11.3 ከመቶ እንደሚያድግ ተተንብዮ የነበረ ቢሆንም ባለፉት 9 ወራት የታየው የውጪ ንግድ ውጤት ግን እንደተጠበቀው አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የግብፅ መንግሥት ወደ ድርድር እንዲገባ ዓለምአቀፍ ጫና እየተደረገበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከሱዳን ጋር የተደረገ አዲስ የወሰን ስምምነት እንደሌለም ገልፀዋል።

በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተናገሩት በብሪታንያና በአየርላንድ የኤርትራ አምባሣደር ተስፋሚካኤል ገራህቱ ምላሽ ሰጥተዋል።
ተስፋሚካኤል ገራህቱ - በብሪታንያና በአየርላንድ የኤርትራ አምባሣደር
ተስፋሚካኤል ገራህቱ - በብሪታንያና በአየርላንድ የኤርትራ አምባሣደር
“ማዕቀቡ ከተጣለ አራት ዓመታት ቢያልፍም በኤርታራ ላይ ምንም ዓይነት ማስረጃ አልቀረበም” ብለዋል አምባሣደሩ።

አምባሣደር ተስፋሚካኤል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “በኤርትራ ላይ ማዕቀብ ከተደነገገ አራት ዓመታት አልፈዋል። ሆኖም እስካሁን ባለው ጊዜ የሶማሊያ ጉዳይንም ሆነ ሌሎቹን በሚመልከት ኤርትራ ላይ ምንም ዓይነት ማስረጃ ለመቅረብ አለመቻሉ ራሱ ትልቅ ማጋለጥ ሆኗል። ስለሆነም ፍትህ የጎደለው ማዕቀብ እንደሆነና መነሳት እንዳለበት በተለያዩ ወገኖችም የሚቀርቡ አመለካከቶችና አቋሞች አሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በኤርትራ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ይካሄድ የነበረው ሴራ አካል ስለሆነ እስካሁን ሲያቀርባቸው የነበሩት ክሦች ሲነጥፉበት ኤርትራ በአሁኑ ወቅት ወደ ጠነከሩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እያመራች በመሆኗ እገዳው ይራዘም የሚለው ይህን ለማሰናከል ነው” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG