በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የቦምብ ጥቃት ያቀነባበሩት ኃይሎች ጥቃታቸውን ሊደግሙ ይችላሉ" - የኢትዮጵያ መንግሥት

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድን ለመደገፍ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ሰልፍ የተፈፀመውን የቦምብ ጥቃት ያቀነባበሩት ኃይሎች ጥቃታቸውን ሊደግሙ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ትላንት ረቡዕ ማስጠንቀቁንና ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተል ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድን ለመደገፍ ባለፈው ቅዳሜ በተደረገው ሰልፍ የተፈፀመውን የቦምብ ጥቃት ያቀነባበሩት ኃይሎች ጥቃታቸውን ሊደግሙ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ትላንት ረቡዕ ማስጠንቀቁንና ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተል ጥሪ ማቅረቡን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

በፍንዳታው ሁለት ሰዎች ተገድለው በርካታ መቁሰላቸው እስካሁን ባለው ጊዜ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ 30 ሰዎች መታሰራቸው የሚታወቅ ነው። ይሁንና ጥቃቱን ያቀደውና ዓላማው ምን እንዳሆነ እስካሁን ባለው ጊዜ አልታወቀም ይላል የሮይተርስ ዘገባ።

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮሙኒኬሽንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ አሕመድ ሺዴ ባለፈው ቅዳሜ በተፈፀመው ጥቃት ያልተሳካላቸው ኃይሎች በሀገሪቱ የተለየዩ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚል ሥጋት እንዳለ በመግልፅ አስጠንቅቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG