በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የቴክኖሎጂ ዘመን በመኾኑ መሳሳትና መዋሸት ጉዳቱ ለራስ ነው” የጋዜጠኝነት መምሕራን


የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሳሳቱ ፎቶዎች መለጠፉን አምኖ ይቅርታ የጠየቀበት
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሳሳቱ ፎቶዎች መለጠፉን አምኖ ይቅርታ የጠየቀበት

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽና በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሠራጩትን የተሳሳቱ ፎቶግራፎች በተመለከተ ባልደረባችን ጽዮን ግርማ “እንዲህ ያሉ ስሕተቶች ምን ያሳያሉ?” የሚል ጥያቄን አንስታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መምሕር አቶ አቤል አዳሙንና በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪገን ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ኮሙዩኒኬን የዶክትሬት ተማሪ አቶ እንዳልካቸው ኃይለ ሚካኤልን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ሠርታልች።

ባለፈው ሣምንት የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል መግለጫን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሠራው የዜና ዘገባ፤ ሚያዚያ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በተካሄደ ዘመቻ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ተላኩ ያላቸውን አሸባሪዎች ካሰባሰቧቸው የጦር መሣሪያዎችና ቁሳቁስ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግሮ ነበር።

ጣቢያው ይህንኑ ዜናም በድረ ገጹ ሲያወጣ በርካታ የጦር መሣሪያ ምስል አያይዞ አሰራጭቷል። የተረጋገጠ መረጃ ለሕዝብ ከሚተላለፍበት መንገዶች አንዱ ፎቶግራፍ ሲኾን ከዚህ ዜና ጋር ተያይዞ የቀረበው የጦር መሣሪያ ምስል ግን በ2004 ዓ.ም በኢራቅ ፋሉጃህ ግዛት በ82ኛው አየር ወለድ ክፍለጦር የተማረከ መኾኑ፤ ፎቶውም የተነሳው “ጌቲ ፒክቸርስ” በተባለ ታዋቂ የአሜሪካ ፎቶ ኤጀንሲ መሆኑ ታውቋል። የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም በእነዚህ ፎቶግራፎች ሲያፌዙባቸው ሰንብተዋል። ይህን ፎቶ በድረገጹ ላይ ተጠቅሞ የነበረው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቂት ቆይቶም ቢኾን ስህተቱን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል።

ባልደረባችን ጽዮን ግርማ እንዲህ ያሉ ስሕተቶች ምን ያሳያሉ? የሚል ጥያቄን አንስታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መምሕር አቶ አቤል አዳሙንና በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪገን ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ኮሙዩኒኬን የዶክትሬት ተማሪ አቶ እንዳልካቸው ኃይለ ሚካኤልን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ሠርታልች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

“የቴክኖሎጂ ዘመን በመኾኑ መሳሳትና መዋሸት ጉዳቱ ለራስ ነው” የጋዜጠኝነት መምሕራን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:43 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG