በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው የኑሮ ጫናውን ያከብደዋል” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
“የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው የኑሮ ጫናውን ያከብደዋል” የአዲስ አበባ ነዋሪዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:47 0:00

በኢትዮጵያ፣ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ፣ አሁን እየታየ ያለውን የኑሮ ጫና ያባብሰዋል ሲሉ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋታቸውን ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹ፣ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ዙርያ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ፣ የትራንስፖርት ወጪን ያንራል፣ በአገልግሎቶችና ሸቀጦች ዋጋ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጭዎቹ፣ መንግሥት የኅብረተሰቡን የኑሮ ኹኔታ የሚያረጋጉ ርምጃዎችን እንዲወስድም ጠይቀዋል፡፡ በነዳጅ ዋጋ ጭማሪውና ርምጃው በፈጠረው ስጋት ዙርያ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ በተያያዘ ዜና፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በዛሬ ውሎው የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ስርዐትን ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG