በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ እዳ፣ ዩሮ ቦንድ እና ቡድን 20


ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ
ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ

ኢትዮጵያ እኤአ በ2014፣ እንደ ፋይናንስ ምንጭና መበደሪያ ይሆናት ዘንድ የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ሸጣለች፡፡ ለሽያጩም በየዓመቱ ከ62 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወለድ ትከፍልበታለች፡፡

የኢትዮጵያ ዩሮ፣ አንዳንዶቹም ዘንድ ዶላር ቦንድ እየተባለ ተፈራርቆ ይጠራል፡፡ ቦንድ ገዥዎቹ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች፣ ኢትዮጵያ ብድርና እዳዎችዋን እንደገና ለማገላበጥና ለመመርመር አቅዳለች የሚለውን ወሬ መናፈሱን ሰምተው መደናገጣቸው ሲዘገብ ሰንብቷል፡፡

የወሬው ምንጭ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮቪድ 19 ያሳደረበትን ጫና ለመቋቋምና ኢኮኖሚውን ማሻሻያ ለመደገፍ የቡድን 20 አባል አገራት ባለፈው ዓመት ህዳር ያወጡትን የጋራ ማዕቀፍ ለመጠቀም ፍላጎት ማሳየቱ መሆኑም ተነስቷል፡፡

ገንዘብ ሚኒስትር ደኤታው ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ አጠቃላይ የእድገት አቅም ጋር በተያያዘ መልኩ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያው እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ሀብት ማሰባሰብ የሚያስችላትን መንገድና አማራጭ ሁሉ ከመጠቀም ወደ ኋላ አትልም፡፡

የኢትዮጵያ እዳ፣ ዩሮ ቦንድ እና ቡድን 20
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:13 0:00


የቡድን 20 አባል አገራት፣ ባላፈው ህዳር ወር ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ፣ በኮቪድና ሌሎች ቀውሶች ኢኮኖሚያቸው የተጎዳባቸው ታዳጊ አገሮች፣ እዳዎቻቸውን መክፈል የሚችሉበትን ድጋፍ ለመስጠት ወስነዋል፡፡

ዶ/ር ኢዮብ እንደሚሉት እገዛው የተደረገው አገራት ብድሮቻቸውን እንዳይከፍሉ ለስማቆም ሳይሆን ቢያንስ እዳቸውን መክፈል የሚችሉበትን የእፎይታ ጊዜ መስጠትን ወይም ማራዘምን ያካተተ ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአይ ኤም ኤፍ ድጋፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች የተሻለ ውጤት የሚያስመዝገቡ አገሮችም የእድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተመልክቷል፡፡

በሌላም በኩል ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 95ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ከዓመታት በፊት ተጀምረው በነበሩት አብዛኞቹ ሜጋ ፕሬጀክቶች ስም፣ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በብድር መልክ የወሰዱት ከፍተኛ እዳ መኖሩን አመልክቶ ነበር፡፡

የፕሮጀክቶቹ ባለቤት የሆኑት የመንግሥት ድርጅቶችም ይህን እዳ መክፈል አልቻሉም የሚል መግለጫም አውጥቷል፡፡

በዚህ የተነሳም የኢኮኖሚ ስብራት መግጠሙን ገልጾ እዳዎቹን ማስተዳደርና ከማነቆው ተላቀው የተሻለ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ወደ ተሻለ አቋም ማሸጋገር ስለሚቻልበት ሁኔታ ውሳኔዎች ማሳለፉንም አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG