አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ ተከስቶ በቆየው ድርቅ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር፣ ከ7.8 ሚሊዮን ወደ 8.5 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡ የተከለሰው የሰብዓዊ ድጋፍ ሰነድ እንዳመለከተው፣ የበልግ ዝናብ በተጠበቀው ደረጃ አልዘነበም፣ በሶማሌ ክልል የቀጠለው የእንስሳት ሞትም ሁኔታውን አባብሷል፡፡
አዲሱ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰነድ ኤችአርዲ በአለፈው ጥር ወር ይፋ የተደረገውን የከለሰና ማሻሻያ ያደረገ ነው፤ በዚህም መሰረት ጥር ላይ 5.6 የነበረው በኋላም ወደ 7.8 ያደገው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር አሁን 8.5 ሚሊዮን መድረሱ ተጠቁሟል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ