ኢትዮጵያ ባለፈው የካቲት ወር የምግብ እርዳታ የጠየቀችው 2.8 ለሚሆኑ ሰዎች ነብር። ይህም ባለፉት አመታት ከነብረው ያነሰ ነው። ይሁንና እስከ ሚያዝያ ወር በነበረው ጊዜ በአብዛኛው የምስራቅ አፍሪቃ የአርብቶ አደሮች አከባቢዎች የግጥሽ መሬቶች በመድረቃቸው በኢትዮጵያ 400,000 የሚሆኑ ተጨማሪ ሰዎች ረድኤት እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።
የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት አገልግሎት ቃል አቀባይ አቶ አክሎግ ንጋቱ “በአሁኑ ወቅት ለሶስተኛው ዙር በአንድ ሶስተኛ ያነሰ ገንቢ ምግብ እያከፋፈልን ነው። የበቆሎና የአኩሪ አተር ድብልቅ የሆነ የገንቢ ምግብ እጥረት ስላለብን ልናቀርበው አልቻልንም። ይህን ውሱን ምግብ ለማግኘት ሸሪኮቻችንን እየጠይቀን ነው።” በማለት ስለሁኔታው አስረድተዋል።