በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ 95ሺሕ ሰዎች በጎርፍ መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ


ባለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ 95ሺሕ ሰዎች በጎርፍ መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:40 0:00

ባለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ 95ሺሕ ሰዎች በጎርፍ መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ

ባለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ በተከሠተው የውኃ መጥለቅለቅ፣ ከ560ሺሕ በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን የገለጸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ከእነዚኽም 95ሺሕዎቹ መፈናቀላቸውንና በ93 ወረዳዎች ደግሞ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሠቱን ገልጿል፡፡

የሰብል መሬት መጎዳቱንና እንስሳትም መሞታቸውን፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በምኅጻሩ ዩኤን-ኦቻ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፣ በበልጉ ዝናም የሰዎች ሞትም ማጋጠሙን አስታውሶ፣ የደረሰው አደጋ ግን የተጠበቀውን ያህል የከፋ አይደለም፤ ብሏል፡፡

በበልግ ወቅት ከፍተኛ ዝናም እንደሚኖር አስቀድሞ ማስጠንቀቁን የገለጸው የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በቀጣዩ ወርኃ ክረምትም ከመደበኛ በላይ ዝናም እንደሚኖር አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG