በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወር የወጭ ንግድ የገቢ ግኝት እና የባለሞያ አስተያየት


የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወር የወጭ ንግድ የገቢ ግኝት እና የባለሞያ አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00

የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወር የወጭ ንግድ የገቢ ግኝት እና የባለሞያ አስተያየት

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከላከቻቸው ምርቶች፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ2ነጥብ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን፣ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ በላይነሽ ረጋሳ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳሉት፣ የተገኘው ገቢ የዕቅዱን 70 በመቶ ማሳካት የቻለ ነው፡፡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋራ ሲነጻጸርም፣ የ122 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አለው።

የምጣኔ ሀብት ባለሞያው አቶ ክቡር ገና፣ አገሪቱ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች የምታገኘው ገቢ በየጊዜው እየቀነሰ መምጣቱን ይናገራሉ።

የሰላም ዕጦት፣ የዋጋ ንረት እና የምርታማነት አለማደግ፣ ለተገኘው ገቢ ማነስ ምክንያት መኾናቸውን ጠቅሰው፣ መንግሥት ችግሮችን መፍታት ይኖርበታል፤ ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG