በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድርቅ ያጠቃቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ አከባቢዎች


ኤርትራና ኢትዮጵያ
ኤርትራና ኢትዮጵያ

አቶ ጎመራ ገሰሰ ከሑመራ አከባቢ አቶ ዮሴፍ ብርሀነ ደግሞ ከመንደፈራ አከባቢ በየአከባቢያቸው ስላለው የዘንድሮ የመኸር ሁኔታ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የትግርኛ ክፍል ሲያስረዱ ከባድ ድርቅ እንዳለ ጠቁመዋል። በአከባቢዎቻቸው ከመንግስት የቀረበ ረድኤት እንደሌለ ሁለቱም ሰዎች ገልጸዋል። አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

አቶ ጎመራ በሑመራ አከባቢ ስላለው የመኸር ሁኔት ሲያስረዱ ደከም ያለ ነው ብለዋል።“እኛ አከባቢ ደከም ያለ አዝመራ ነው ያለው። በተደጋጋሚ የተዘገበ ነገር ስለሆነ መንግስትም የሚያውቀው ነገር ነው። ከአደባ አንስቶ እስከ ራውያንና በረኸት በርከት ያለ ህዝብ ችግር ላይ ወድቋል። እስካሁን ባለው ሁኔታ የተደረገ ረድኤት የለም። ምንም አይነት ዝናብ ስላልተገኘ ድርቅ ሰፍኗል። እንስሳትም ወደ መቸገር ገደማ ናቸው። ሰዎች አልፎ አልፎ መሰደደ ጀምረዋል”ይላሉ አቶ ጎመራ።

ሑመራ አከባቢ በአብዛኛው የሚዘራው ሰሊጥና ማሽላ ሲሆን የሰሊጥ ዘር በአብዛኛው በድርቅ ተቃጥሏል። ማሽላውም እንደዚሁ ብለዋል አቶ ጎመራ። ህዝቡም በየስብሰባው የሚናገረው ነገር ነው። ነገር ግን እስካሁን ባለው ጊዜ የተገኘ ምላሽ የለም ሲሉም አቶ ጎመራ አክለውበታል። በወሬ እንደሚሰማው ግን ሑመራ ራሱን የቻለ አከባቢ ነው የሚል አመለካከት እንዳለ አቶ ጎመራ ገልጸዋል።

ኤርትራ ውስጥ መንደፈራ አከባቢ ያሉት አቶ ዮሴፍ ብርሀነ በበኩላቸው ሀምሌ ወር መጨራሻ ላይ ዝናብ ተገኝቶ ነብር። ግን አልቀጠለም ብለዋል። "ሐምሌ ወር ማብቂያ ላይ ዝናብ መጥቶ ነበር። ነገር ግን አልቀጠለም። ጤፍንና ማሽላን የመሳሰሉትን ነው የምንዘራው። አብዛኛው ሳያድግ ስለጠፋ እንስሶች እንዲግጡት ተደርጓል። ይህ ሲባልም ከቦታ ቦታ ይለያያል። በአንዳንድ ቦታዎች ትንሽ መኸር ያስገቡ ይኖራሉ። በአብዛኛው ግን ከብት ተለቆበታል" ሲሉ አቶ ዮሴፍ ብርሀነ አስረድተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG