ህወሓት ኤርትራ ላይ ያደረሰውን ጥቃት እና እየተካሄደ ያለውን ግጭት ዓለማቀፋዊ ለማድረግ ያደረገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ተናግረዋል።
ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ለማብረድ ሰላምን መልሶ ለማስፈን እና የሲቪሎችን ደኅንነት ለመጠበቅ አስቸኳይ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እናሳስባለን ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዎ በትውዊተር ገጻቸው ባወጡት ጽሁፍ አሳስበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ውጊያው መቀጠሉንና የህወሓት ሃይሎች አስመራ ላይ ያደረሱትን የሮኬት ጥቃት ተከትሎ ብሪታንያ በአስቸኳይ ግጭቱ እንዲበርድ የሲቪሎች ደኅንነት እንዲጠበቅ ጥሪ አቅርባለች።
የብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳይ ሚኒስትር ጄምስ ደድሪጅ በውጊያው ለተጎዱ ሲቪሎች እርዳት መድረሱን ለማረጋገጥ ከረድዔት ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራን ነን ብለዋል።