በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል የተኩስ አቁምና የተከተሉት እሰጥ አገባዎች


የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሃይሎች "ጠላት" ሲሉ የጠሩዋቸውን ኃይሎች አስፈላጊ ከሆነ ኤርትራ ግዛት እና አማራ ክልል ገብተው ያሳድዳሉ ማለታቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

የህወሓት ቃል አቀባዩ ዋናው ትኩረታችን የጠላትን የውጊያ ዐቅም ማሽመድመድ ነው፤ ያን ለማድረግ ደግሞ አማራ ክልል መግባት ከአለብን እንገባለን ኤርትራ ግዛት መግባትም ካለብን እንገባለን ሲሉ ዛሬ ከቀትር በኋላ ለሮይተርስ በሳተላይት ቴሌፎን በሰጡት ቃል መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት “የአማራ ሕዝብ በሽብርተኞች ሂሳብ እንዲወራረድበት አይፈቅድም" የሚል መግለጫ ማምሻውን አውጥቷል። ህወሓትን “አማራን ህዝብ በአጠቃላይ የሚጠላ ቡድን ነው” ሲል ከስሷል።

መግለጫው አክሎ “የአማራ ሕዝብ የትኛውንም በቀል ለመበቀል ፍፁም አልተዘጋጀም። ይህ ማለት ግን "ሂሳብ እናወራርዳለን" ባዮችን በዝምታ ይታገሳል ማለት አይደለም። ከዳተኛና ጸረ-ሕዝብ የሆኑ የትኞቹንም ጠላቶቹን ያለ ምህረት ይታገላል” ብሏል።

“ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ በራሳቸው መስዋትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃችኋለን። እነዚህን አካባቢዎች ከሕግ ውጭ በጉልበት ወስዶ ለመጠቅለል ፍላጎት ካለ፣ ለነፃነቱ ሲል ዋጋ የማይከፍል አማራ የሌለ መሆኑን ደግመን ደጋግመን እናረጋግጥላችኋለን” ብሏል የአማራ ብልፅግና።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ህወሓት እና ተባባሪዎቻቸው ኢግሪ መትከል፣ አዲ ቤጊያዮ፣ አሰብ እና ጾረና ግንባር ከዚያም በቅርቡም የደረሰባቸውን ወታደራዊ ሽንፈት ታሪክ መለስ ብለው የመመልከት አቅም የሌላቸው ናቸው፣ አሁንም “ጌም ኦቨር” አለቀ ደቀቀ ሲሉ ምን ማለት እንደሆን አያውቁትም ሲሉ ጽፈዋል።

XS
SM
MD
LG