በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጠው ምፅዋና አሰብ የሚያደርሱ መንገዶችን መክፈት መሆኑ ተገለፀ


ከኢትዮጵያና ከኤርትራ እርቀ-ሰላም በኋላ ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጠው ወደ ምፅዋና አሰብ የሚያደርሱ መንገዶችን ለመክፈት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከኢትዮጵያና ከኤርትራ እርቀ-ሰላም በኋላ ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጠው ወደ ምፅዋና አሰብ የሚያደርሱ መንገዶችን ለመክፈት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ወደየትኛውም አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ የሚፈልጉ የሁለቱ ሃገሮች ዜጎችም ቪዛ በቅድሚያ ማግኘት እንደማይጠበቅባቸውና ሁለቱም ሃገሮች ውስጥ የሁለቱን ሃገሮች ፓስፖርቶች የያዙ ተጓዦች እንደደረሱ ቪዛ እንደሚሰጣቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ባሠራጩት መልዕክት አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በምፅዋና በአሰብ ወደቦች ክፍት መሆን የሚጠቀሙት የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብቻ ሳይሆኑ መላው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ መሆኑንም የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ሺዴ ዛሬ ማመልከታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በዌብ ሳይቱ ላይ አስፍሯል።

የአሰብና የምፅዋ ወደቦች ለሥራ ክፍት መሆን የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሃገር የሆነችውና የራሷ የባሕር በር የሌላት ኢትዮጵያ ወጭ ንግዷን ለማቀላጠፍና የውጭ ምንዛሪ ጥሪቷንም ለማሳደግ ያላትን ጉጉት በብዙ እንደሚያግዝ የሮይተርስ ዘገባ ይጠቁማል።

ኢትዮጵያ በአመዛኙ በወጭና ገቢ ንግዷ በአመዛኙ በጅቡቲ ወደብ ላይ ተመርኩዛ የቆየች ብትሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በቅርቡ ኻርቱም ተገኝተው በነበረ ጊዜ ፖርት ሱዳንንም ለመጠቀም ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር ተነጋግረው እንደነበረ ዘገባው አስታውሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG