በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ውስጥ በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ


የኢትዮጵያ ወታደሮች
የኢትዮጵያ ወታደሮች

የኢትዮጵያ መንግሥትኤርትራ ውስጥ በ“ሽብርተኞች” ማሠልጠኛዎች ላይ ጥቃት አደረስኩ አለ፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ የሽብርተኛ ጣቢያዎች ማሠልጠኛ ሠፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሱን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሽመልስ ከማል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ንጋት ላይ ኤርትራ ግዛት ውስጥ ከኢትዮጵያ ወሰን ከአስራ ስድስት እስከ አስራ ስምንት ኪሎ ሜትሮች ዘልቆ ገብቶ በሦስት ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሠፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሱን አቶ ሽመልስ ገልፀዋል። ጥቃቱም የኤርትራ መንግሥት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ አደረሰ ያሉት አፀፋ እንደሆነ ተናግረዋል። አቶ ሽመልስ በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት ዝርዝር ወደፊት ይገለጣል ብለዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ በጉዳዮ ላይ መልስ እንዲሰጡ የጠየቃቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አሊ አብዱ “ቀድሞ ተደበደብኩ ብሎ ይጮህ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን ደግሞ ደበደብኩ እያለ ነው” አገዛዙ አገር ውስጥ ባሠፈናቸው ጠባብ ፖሊሲዎች ምክንያት ለገጠሙት ችግሮች የውስጥ ቀውሶችን በምክንያትነት ያቀርባል ብለዋል።

አዲስ አበባ ያለው መንግሥት የውጭ ኃይሎችን ጥቅም ለማስጠበቅ አካባቢአዊ አለመረጋጋት አስፍኗል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በሦስቱ የኤርትራ ጦር ሠፈሮች ውስጥ ጥቃት ማድረስ ያለማድረሱን በተመለከተ ግን ዝርዝር መረጃ ገና ከእጃችን አልገባም ብለዋል።

በተያያዘ ዜና የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት መሪ አጋስ አሕመድ ኑር ከቤልጅየም በሰጡን ቃል “የኢትዮጵያ ኃይሎች የአፋር ሸማቂ ኃይሎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የውስጥ ምንጮች ገልፀውልኛል” ሲሉ አረጋግጠዋል።

የዘገባውን ዝርዝር ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG