በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ህወሓት እና የኤርትራ ወታደሮች በስደተኞች ላይ የጦር ወንጀሎች ፈፅመዋል" - ህዩማን ራይትስ ዋች


ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ህዩማን ራይትስ ዋች ወራትን ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ ኤርትራዊያን ስደተኞች አስገድዶ መደፈርን እና ግድያን ጨምሮ እጅግ ብዙ በደሎችን እየደረሱባቸው መሆኑን ገልፆ ሪፖርት አወጣ፡፡

የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር፤ “በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራዊያኑ ስደተኞች ቀድሞውንም ከሃገራቸው እንዲሰደዱ ባደረጓቸው የኤርትራ ወታደሮች እና ድርጅቱ የትግራይ ኃይሎች ብሎ በጠራቸውና የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ብሎ በጠራቸው የሕወሃት ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል።" ያሉ ሲሆን አያይዘውም

"በትግራይ ክልል በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ግድያ፣ አስገድዶ መደፈርና ዝርፊያ ግልጽ የሆነ የጦርነት ወንጀል ነው፡፡" ብለዋል፡፡

ከዩናይትድ ስቴትስ የተጠናቀረው ሪፖርት ኤርትራዊያን ስደተኞች በትግራይ ኃይሎች እና በኤርትራዊያን ወታደሮች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የማስገደድ እና የሚኖሩቧቸውንም ሁለት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ማውደምን የመሳሰሉ ችግሮችና በደሎች እንደደረሱባቸው አካቷል፡፡

የሂውማን ራይትስ ዋች የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ለቲሽያ ባደር "በትግራይ ክልል በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ግድያ፣ አስገድዶ መደፈርና ዝርፊያ ግልጽ የሆነ የጦርነት ወንጀል” ብለዋል።

ሪፖርቱ እ.ኤ.አ ከሕዳር 2020 ዓ.ም አንስቶ እስከ ጥር 2021 ዓ.ም ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰደተኞችን በሚይዙ የሕጻጽ እና ሽመልባ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች በኤርትራ እና በትግራይ ሃይሎች በፍርርቅ ተፈጸሙ የተባሉ በደሎችን የያዘ ሲሆን የ28 ኤርትራዊ ስደተኞችን ቃለመጠይቅ እና የሳተላይት ምስሎችን በምንጭነት መጠቀሙን አስታውቋል፡፡

በምርመራው ላይ የኢትዮጵያ የስደተኛ እና ከስደት ተመላሾች አስተዳደር ፣ የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ዩኤን ኤች ሲ አር እንዲሁም በተመድ የኤርትራ ቋሚ ልዑክን ማብራሪያ መጠየቁን አመላክቶ ነገር ግን ከኤርትራ ምላሽ ባለማግኘቱ አለማካተቱን አስታውቋል፡፡ ይሁንና የኤርትራ መንግሥት ከዚህ ቀደም በዚህ ጉዳይ ላይ ንጹሃን ዜጎችን እና ሰደተኞች ላይ ላይ ይደርሳል የተባለውን ጥቃት አስተባብሏል፡፡

በተመሳሳይ ሕውሃት በበኩሉ መደበኛ የትግራይ ሃይሎች ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሱት በቅርቡ መሆኑን በመግለጽ የተፈጸሙት በደሎች በሙሉ በአካባቢው ባሉ የኤርትራ ሚሊሺያዎች የተፈጸሙ ናቸው ሲሉ ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም

“አጋጣሚዎቹን በመጠቀም የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ከነበሩ ያንን ለማስቆም አንችልም” ሲሉም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ህዩማን ራይትስ ዋች ባቀረበው ሪፖርት የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽንን ጠቅሶ ከ20,000 ስደተኞች ውስጥ ከሽመልባ እና ከሕጻጽ የስደተኛ ካምፖች 7,643ን ስደተኞች መጥፋታቸውን ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽን ዩኤን ኤች ሲ አር በስደተኞች ካምፑ ውስጥ የተፈጸመውን ከፍተኛ ግፍ አስደንጋጭ ነው ሲል የጠራው ሲሆን በስደተኞቹ ካምፑ ውስጥ የነበሩትን ስደተኞች ከባለፈው ሕዳር ወር አንስቶ እስከ መጋቢት ድረስ ማግኘት አልቻልንም ነበር ብሏል፡፡ኮሚሽኑ አያይዞም በአሁን ሰዓትም

“በደቡባዊ ትግራይ ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ የሰደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ስላሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ሁኔታ ተጨንቀናል” ሲሉ ለሮይተርስ አስታውቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

"ህወሓት እና የኤርትራ ወታደሮች በስደተኞች ላይ የጦር ወንጀሎች ፈፅመዋል" - ህዩማን ራይትስ ዋች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:57 0:00



XS
SM
MD
LG