የኢትዮጵያ መንግስት በሰመራ “አበላ” በተሰኘው መንገድ ላይ የእርዳታ እሕል በጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በህወሃት ተፈጸመ ያለውን ጥቃት አወገዘ፣ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚል ስሌት የእርዳታ አቅርቦት እያስተጓጎለ ይገኛል ያለውን ህወሓት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጭምር ሊያወግዘው ይገባል ብሏል። በሰመራ መስመር በኩል ወደ ትግራይ ሊላክ የተዘጋጀ የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰላም እጦት ሰመራ ከተማ ላይ ቆመው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም አስታውቋል። ከሰኔ 11/2013 ዓ.ም ወዲህ የመጀመሪያውን የሰዎች በረራ ወደ መቀሌ ማድረጉንም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
በሌላ ዘገባ ደግሞ በኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ «ህወሃት» የስደተኛኛ መጠለያ ጣቢያዎች ወዳሉባቸው አካባቢዎች መግባቱን ተከትሎ እስካሁን ድረስ ቢያንስ ስድስት ስደተኞች እንደተገደሉ የሚያሳዩ መረጃዎች ማግኘቱን ገልጦ ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ አስከፊ እና አሳሳቢ ወደ ሆነ ደረጃ እየተሸጋገረ መሄዱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በሌላ በኩል በዘገባዎቹ ውስጥ ስሙ የተነሳው ሕወሃትን ወይም አሁን ትግራይን ተቆጣጥረው ካሉ ወገኖች ምላሽ ለማግኘት ባደረግነው ጥረት በውጭ ኦፊሴላዊ ተጠሪ መሆናቸው የተነገረውን አምባሳደአር ፍሰሃ አስገዶምን የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በትረ ሥልጣን ደውሎ አነጋግሯቸዋል።
የእርዳታ አቅርቦትና የተያያዙ ችግሮችን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
(አዲስ ቸኮል፣ ዮናታን ዘብዲዮስና የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባ በትረ ሥልጣን ያጠናቀሯቸውን ዘገባዎች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)