በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ የኤርትራ ወታደሮች ይወጣሉ አሉ


ፎቶ ፋይል፦ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ
ፎቶ ፋይል፦ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ

የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በእርግጠኝነት በቅርብ ጊዜ ይወጣሉ ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ ተናገሩ።

ቋሚ መልዕክተኛው ይህ ያሉት አንድ ከፍተኛ የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን ኤርትራዊያኑ ወታደሮች ረሃብን በጦርነት መሳሪያነት እየተጠቀሙበት ናቸው በማለት ለጸጥታ ምክር ቤቱ ያደረጉትን ገለጻ ተከትሎ ነው።

ተሰናባቹ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ረድዔት ጉዳዮች ሃላፊ ማርኮ ሎውኮክ በዝግ ለተከናወነው የምክር ቤቱ ስብሰባ ባደረጉት ገለፃ፣ የትግራይ ሁከት ካልቆመ ኤርትራውያን ወታደሮችም ካልወጥ የ1984ቱን የመሰለ ከባድ ረሃብ ቢደገም ማንም ሊገረም እየገባም ብለዋል።

አስገድዶ መድፍር፣ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ለማሽበር ጥቃት ሥራ ላይ እየዋለ ነው ያሉት ማርክ ሎውኮክ የኤርትራ ወታደሮች ረሃብን ለጦርነት መሳሪያ አድገውታል፣ ተፈናቃዮች ይታፈሳሉ፣ ይደበደባሉ፣ ይዋከባሉ ማለታቸውን ሮይተርስ ስብሰባው ላይ የተገኙ ዲፕሎማት ጠቅሶ ዘግቧል።

በኒው ዮርክ የተመድ የኤርትራ ሚሲን ለባለሥልጣኑ ገለጻ ምላሽ ለጊዜው አልሰጠም። ይሁን እና ኤርትራ ወታደሮችዋን ማስወጣት ልትጀምር መስማማትዋን ባለፈው ሚያዝያ አስታውቃ እንደነበር ይታወሳል፥ በድርጅቱ የኢርትራ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋ ማርያም በዚያ ወቅትም ወታደሮቹ ወሲባዊ ጥቃትን ህዝብ የማስራብ ተግባር እየፈጸሙ ነው የሚለውን ክስ አስተባብለው ነበር።

የጸጥታ ጥበቃው ግለጻ ወቅት የተገኙት የኢትዮጵያ ቁዋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታየ አዝቀ ስላሴ የኤርትር ወታደሮች አንዳንድ ቴክኒካዊ እና የሂደት አፈጻጸም ጉዳዮች እስኪስተካከሉ ነው እንጂ በቅርቡ ይወጣሉ ብለን የምንጠብቀው ሲሉ ከስብሰባው በኋል ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ማርክ ሎውኮክ ገለጻውን ያደረጉት ትግራይ ውስጥ ከሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎች በረሃብ ሁኔታ ላይ ናቸው የሚል ግምገማ ሪፖርት በድርጅቱ መስሪያ ቤቶችን በረድዔት ቡድኖች መሰጠቱን ተከትሎ ነው በአስር ዓመት ውስጥ ያልታየ ከባድ የምግብ ዕጥረት ሲሉ ገልፀውታል፥ የከበደ የምግብ ዕጥረት የለም፣ እርዳታም እየተሰጠ ነው በማለት አስተባብለዋል።

XS
SM
MD
LG