በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ወደ አስመራ ተመለሱ


ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሦስት ቀን የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አስመራ የሚመለሱትን የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂን አሸኛኘት ሲያደርጉ
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሦስት ቀን የሥራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አስመራ የሚመለሱትን የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂን አሸኛኘት ሲያደርጉ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት ያደረጉትን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ወደ አስመራ ተመልሰዋል።

ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሃገራቱ የሁለትዮሽና የቀጠናው ጉዳዮች ላይ በመመካከር የተጀመሩ ግንኙነቶችን ለማሳደግ መስማማታቸውን የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስትር የማን ገ/መሥቀል በትዊተር ገፃቸው አስፈረዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሣያስና አብረዋቸው የተጓዙት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ቆይታችው በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የልማት ቦታዎችን ጎብኝተዋል።

የጅማ ዩኒቨርስቲ፣ የኮይሻ እና የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን እና የእንጦጦ ፓርክ ከተጎበኙት መካከል ናቸው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ወደ አስመራ ተመለሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:55 0:00


XS
SM
MD
LG