በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቆይታ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ጋር


አቶ ፍጹም አረጋ
አቶ ፍጹም አረጋ

“የሁለቱ አገሮች የሰላም ስምምነት ለአካባቢው አገሮች፣ በአጠቃላይም ለአፍሪካ ቀንድና ለመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ፤ምሳሌም ስለሆነ፣ በዚህም የተነሳ የተባበሩት አረብ ኤሜሬት የሁለቱ አገሮች መሪዎች ባደረጉት አስተዋጾ ይህን ሽልማት ማበርከታቸውን በሽልማቱ ወቅት ገልጠዋል።”የጠቅላይ ሚንስትሩን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ አገሮች መሃከል የተካሄደውንና ደም ያፋሰሰውን ጦርነት ተከትሎ ለተፈጠረው አስርታት የዘለቀ ሰላም አልባ ጊዜ ማብቂያ ለማበጀት ላበረከቱት አስተዋጾ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትን ከፍተኛ ሽልማት ተቀበሉ።

በሌላ በኩል የምጽዋ ወደብ ለኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ንግድ ዝግጁ መሆኑ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ በሀገሪቱ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችን ወደ ጽ/ቤታቸው ጋብዘው በልዩ-ልዩ ወቅታዊ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ አወያይተዋል። የዜና ዘገባዎቹን መነሻ በማድረግ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋን አወያይተናል።

ቆይታ ከጠቅላይ ሚንስትሩን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ጋር .. ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG