በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግስት ሥልጣን የያዘበት 20ኛ ዓመት ነገ ይከበራል


መንግስት በሁለቱ አስርተ ዓመታት የህዝቡን ህልምና ምኞት ለማሳካት በርካታ ክንዋኔዎች ተመዝግበዋል ይላል፣ ተቃዋሚዎች ግን ለብዙዎች ያመጣዉ መሻሻል የለም ይላሉ

ማርክስት ሌኔንስት የትግራይ ሸማቂዎች በኢትዮጵያ ሥልጣን የያዙበት ሃያኛ ዓመት ነገ ሊከበር መስቀል አደባባይ በወዜማዉ ባዶና ጭር ያለ ነዉ። ጥቂት ሰራተኞች ብቻ ነገ ንግግር የሚደረግባቸዉ መድረኮችና የድምጽ ማጉያዎችን ማዘጋጀት ይዘዋል።

በ1983 ዓም አምባገነኑ የደርግ መንግስት የተወገደበትንና መሪዉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም ወደ ዝምባብዌ የኮበለሉበትን 20ኛ ዓመት ለማክበር ነገ ማለዳ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ወደ መስቀል አደባባይ ይጎርፋሉ። የመንግስት ኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፣ በእነዚህ ሁለት አስርተ ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ህልምና ምኞት ለማሳካት በርካታ ክንዋኔዎች ተመዝግበዋል፥ የሕዝቡ ኑሮ በእጅጉ ተሻሽሎአል ይላሉ።

በዚህች 90 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ በሚኖርባት አገር በመንግስት ሥራ ያልረኩም አሉ። በመስቀል አደባባይ ቆመዉ ተሳፋሪ ይጠባበቁ የነበሩ ታክሲ አሽከርካሪዎች ለምሳሌ ነገ ቅዳሜ ተቃዉሞአቸዉን በመግለጽ ቤት እንደሚዉሉ ተናግረዋል።

የሰላሳ ሁለት ዓመት እድሜ ያለዉ ዘርይሁን ጌትዬ መለስ ዜናዊ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የብዙሃኑ ኢትዮጵያዉያን ሕይወት ምንም አልተሻሻለም ይህ መንግስት ለአንዳንዶች ኑሮ ጥሩ ነዉ ለእኔና ብዙሃን ግን ያመጣዉ ለዉጥ የለም ይላል።

የኢንተርኔት ማህበራዊ መገናኛ ድረ ገጾችን የሚጠቀሙ የመንግስት ተቃዋሚዎች ነገ ቅዳሜ ከመንግስት በዓል ትይዩ ጸረ መንግስት ተቃዉሞ እንዲካሄድ ጥሪ አድርገዋል። ”በቃ” በሚል መገለጫ የሚታወቀዉ ተቃዉሞ፣ በሰሜን አፍሪቃዉ ሕዝዊ መነሳሳት መልክ ነዉ የታቀደዉ ነዉ ተብሎአል። የቪኦኤ ዘጋቢ Peter Heinlein ከአዲስ አበባ የላከዉን ሪፖርት፣ ያዳምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG