የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ በዐዲስ አበባ ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ጋራ የመጀመሪያውን ውይይት አደረገ፡፡
የዳያስፖራ አባላቱ፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማምጣት ከኮሚሽኑ ጋራ አብሮ መሥራት አስፈላጊ እንደኾነ ገልጸው፣ ተቋሙም ሓላፊነቱን ለመወጣት፣ ከመንግሥት ተጽእኖ ነጻ እና ገለልተኛ ኾኖ እንዲንቀሳቀስ ጠይቀዋል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ በበኩላቸው፣ ኮሚሽኑ ሥራውን በነጻነት የሚያከናውን ገለልተኛ ተቋም እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ በምምክር ሒደቱ፣ ኹሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸው፣ በየአካባቢው ያሉ የታጠቁ ኀይሎችም፣ ጥያቄያቸውን ለኮሚሽኑ እንዲያቀርቡ እያበረታታን ነው፤ ብለዋል፡፡
ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ የምክክር ልምድ መቅሰም እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ዋና ኮሚሽነሩ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም፣ የምክክር ሒደቱ አካል እንደሚኾኑ አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም