ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ከነዚህም ውስጥ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በግጭት ምክንያት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ናቸው ብሏል የኮሚሽኑ ሪፖርት።
በውይይቱ ወቅትም ለአስቸኳይ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ዕርዳታ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈል ተገልጿል።
ከሚያስፈልገው ገንዘብም የኢትዮጵያ መንግሥት 60 በመቶውን የሚሸፍን ሲሆን፣ ቀሪውን 40 በመቶ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ለጋሽ ድርጅቶች ለመሰብሰብ መታቀዱም ታውቋል። ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት ለአስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ 342 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የመደበ ሲሆን፣ ለጋሽ ድርጅቶች ደግሞ 595 ሚሊየን ዶላር አስተዋፅዖ ማድረጋቸው ይታወሳል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ