እስከዛሬ ድረስ በታየው የምርጫ 2007 ሂደት አስከፊ ያሉዋቸው ገጽታዎች ቢኖሩም ህዝቡ የሚፈልገውን ዲሞክራሲያዊ ሂደት ለመደገፍ ፓርቲያቸው ዝግጁ መሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አለጥርጥር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግርን እንደሚፈልግ ፓርቲአቸዉ መረዳቱን ጠቁመዉ በምርጫዉ የሚሳተፈዉም ባለዉ ቀዳዳ ለመጠቀምና ሕዝቡንንም ለማስተማር ነዉ ብለዋል።
በነገዉ እለት አዲስ አበባ ዉስጥ በስምንት መኪናዎች ቅስቀሳ ማድረግ እንደሚጀምርና ለምርጫዉ ታዛቢዎችንም እንደሚያቀርብ አቶ ይልቃል ተናግረዋል። በምርጫዉም የሚሳተፈዉ በዚሁ ምክንያት ነዉ ብለዋል።
በመንግስት በኩል የሚወሰዱት አንዳንድ ርምጃዎች እና መግለጫዎች ስጋትና ሽብርን የሚፈጥሩ ናቸዉ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የፓርቲው ንቁ አባላትና ደጋፊዎች ዛሬም በጅምላ እየታሰሩ ናቸው ሲሉም አማርረዋል።