በቅርቡ የተካሄደውን አነጋጋሪውን የኢትዮጵያ የፓርላማ ምርጫ ውጤቶች ይፋ መሆን ተከትሎ ጠንከር ያሉ የግምገማ አስተያየቶች ከያቅጣጫው እየተሰሙ ነው።
በውድድሩ ተሳትፈው በየትኛውም የምርጫ ጣቢያ አሸናፊ የሚያደርጋቸውን ድምጽ እንዳላገኙ ያመላከተውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የውጤት መግለጫ አንድምታ አስመልክቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ልዩ ልዩ ትችቶች እየሰነዘሩ ነው። ይህንኑ ተንተርሶም ሁለት የእሰጥ አገባ ተሳታፊዎች የምርጫውን ውጤት ምንነትና የወደፊት አቅጣጫዎች የተመለከቱ የሁለትዮሽ እይታዎች የተንጸባረቀበት ክርክር ይዘዋል።
ተሳታፊዎቹ፥ አቶ ንጉሴ ቢራቱ የሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ነዋሪ በግል ሥራ የሚተዳደሩ፤ አቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና፥ በዩናይትድ ስቴትስ የጤና ምርምር ተቋም የምርምር ሠራተኛና እርሳቸውም የሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ነዋሪ ናቸው።