በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ


የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሣን ሻራፍ ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ መለስ ዜናዊና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ እንደምትሠራ ከገለፀች ወዲህ ግብፃዊያኑ ወደአዲስ አበባ ሲሄዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛቸው መሆኑ ነው፡፡ በቅርቡ ወደኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የግብፅ የሕዝባዊ ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድን ሰፋ ያሉ ውይይቶችን አድርጎ ተመልሷል፡፡

የአሁኑ ጎብኝ ደግሞ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሣን ሻራፍ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት ከውይይቱ ርዕሶች አንዱ የአባይ ግድብ ነው፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG