ዋሺንግተን ዲ.ሲ.- አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያና የግብፅ የውኃ ሚኒስትሮች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ያደረጉት ስብሰባ ያለስምምነት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ለቪኦኤ ዛሬ ማምሻውን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ግብፅ በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያላት አቋም የፀና በመሆኑ ምክንያት የዛሬው ዓይነት ስብሰባ የሚያመጣው የመቻቻል ለውጥ ሊኖር እንደማይችል የግብፁ ሚኒስትር መናገራቸውን አንድ የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ እና በግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ዶ/ር ሞሐመድ አብደል ሙታሊብ መካከል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ የተካሄደው ስብሰባ ሃሣብ የቀረበው በግብፅ መገናኛ ብዙኃን እንደተዘገበው በኢትዮጵያው ሚኒስትር ጥያቄ አለመሆኑን አቶ ዓለማየሁ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ግብፅ አቋሟ የማይለሳለስ መሆኑን በተደጋጋሚ በምታወጣቸው መግለጫዎች የምታሣውቅ ሲሆን በተለይ “ታሪካዊ መብቴ” የምትለውን ከናይል 84 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የዓመት ፍሰት “55.5 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትሩን በዓመት መጠቀም እንደምችል ማረጋገጫ ካልተሰጠኝ በማንኛውም የናይል ተፋሰስ ስምምነትና ትብብር ውስጥ አልገባም” ስትል ትሰማለች፡፡
ኢትዮጵያም በበኩሏ በኅዳሴ ግድብ ግንባታ እንደቀጠለች ነው፡፡
የግብፁ አል አህራም የአረብኛ የኢንተርኔት ዜና ማሠራጫ “ኢትዮጵያ ምናልባት ተስፋ እንደምታደርገው በኅዳሴ ላይ የምንለሳለስበት ወይም የምንቻቻልበት አቋም የለም” ሲሉ የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል ሙታለብ መናገራቸውን ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያው ሚኒስትር ዓለማየሁ ተገኑ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ እንዲህ ዓይነቱ እሰጥ አገባ ወደ ሌላ መካረር ይወስዳል የሚል ሥጋት እንደሌላቸው ጠቁመው ብቸኛው አማራጭ በትብብር መሥራት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያየዘውን ዘገባ እና ከኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ ሙሉ ቃል ያዳምጡ፡፡