በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያና የግብፅ መሪዎች የማላቦ ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ /ማላቦ - ኢኳቶሪያል ጊኒ - ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ /ማላቦ - ኢኳቶሪያል ጊኒ - ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

የኢትዮጵያና የግብፅ መሪዎች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ሰሞኑን በግንባር ተገናኝተዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያና የግብፅ መሪዎች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ሰሞኑን በግንባር ተገናኝተዋል፡፡

ኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ ማላቦ ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጉባዔ ጎን ሁለቱ መሪዎች ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ይህንን ባለፈው ሣምንት ሐሙስ የተካሄደውን የሁለቱን መሪዎች ውይይት ተከትሎ የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ባወጡት ዜና ሃገሮቹ በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ የሚሠራ አንድ የጋራ ኮሚቴ በመጭዎቹ ወራት ውስጥ ለማቋቋም መስማማታቸውን ዘግበው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በሰባት ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀው በተባለው ኮሚቴ ላይ ግን የተደረሰ ስምምነት አለመኖሩን ገልፀዋል፡፡

መሪዎቹ ከተግባቡባቸው ነጥቦች መካከል የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ንግግሮች እንደገና መጀመር እንደሚገኝበት ታውቋል፡፡

የግብፃዊያን የኅዳሴ ግድብ ግንባታ ይጎዳናል ሲሉ ቆይተዋል፤ አሁንም በአቋማቸው እንደፀኑ ናቸው? የግብፅ መሪዎች ከናይል ተፋሰስ ሃገሮች የትብብር ተቋም ጋር ያላቸው ግንኙነት የተቀዛቀዘ ነው፤ አሁንም በአቋማቸው እንደፀኑ ናቸው?

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG