በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ዙሪያ ያነሳችው ሃሳብ


ታላቁ የኅዳሴ ግድብ
ታላቁ የኅዳሴ ግድብ

ግብፅ በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ላይ የምታነሳቸው ሀሳቦች፣ የኢትዮጵያን ቀይ መሥመር የሚያልፍ ነው ስትል ኢትዮጵያ አስገንዝባለች።

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ተፈራ በየነ፥ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል እየተደረገ ባለው የሦስትዮሽ ውይይት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሚያካሄዱት ድርድር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል የምትለው ግብፅ በበኩልዋ ዓለምቀፍ ሽምግልና እንዲገባበት ጥሪ አድርጋለች።

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በሦስቱ ሀገሮች ድርድር ውስጥ ዓለምቀፍ ሽምግልና እንዲገባ መጠየቁን አውግዞ የግንባታውን ሂደት ያሰናክላል ብሏል። ዩናይትድ ስቴትስ በበኩልዋ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ወሀ መሙላትንና ሥራው ማስቀጥልን አስመልክቶ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በትብብር፣ በዘላቂነትና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሥምምነት እንዲያደርጉ እንደምትደግፍ ገልፃለች።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ግብፅ በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ዙሪያ ያነሳችው ሃሳብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG