በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፋር ክልል እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ እንደሚችል  ምልክቶች መታየታቸውን ዛሬ  የከርሰ ምድር ጥናት አስታወቀ 


በአዋሽ ፈንታሌ ጭስ ሲወጣ የሚያሳየው የቪዲዮ ምስል
በአዋሽ ፈንታሌ ጭስ ሲወጣ የሚያሳየው የቪዲዮ ምስል

በኢትዮጵያ አፋር ክልል፣ አዋሽ ፈንታሌ የእሳተ ገሞራ መፈንዳት ምልክቶችን እንዳሳየ የኢትዮጵያ ከርሰ ምድር ጥናት ተቋም ዛሬ ዐርብ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ከአጭር ቪዲዮ ጋራ ባጋራው መረጃ አስታወቀ። ተቋሙ በአዋሽ ፈንታሌ ጭስ ሲወጣ ከሚያሳየው የቪዲዮ ምስል ጋራ ባጋራው መረጃም፣ "ሰሞኑን ሲጠበቅ የነበረው አዋሽ ፈንታሌ በአሁኑ ሰዓት በአፋር ክልል ዱላቻ ወረዳ ዳፋን ተራራ ላይ የታመቀ ውሃ እና እንፋሎት ተከሰተ" ብሏል።

በዚህም ምክኒያት ባለሥልጣናት ነዋሪዎችን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲያዘዋውሩ ማድረጋቸውን የሀገር ውስጥ ብዙኅን መገናኛ ዘግበዋል። በመንግሥት የሚደገፈው ፋና ብሮድ ካስቲንግ በአፋር ክልል የጋቢ ረሱ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ ዓሊ ጠቅሶ በአወጣው ዘገባ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ነዋሪዎችን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማጓጓዝ ሥራ እየተሠራ መኾኑን ጠቅሷል።

"ፍንዳታ ለመሆኑ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም፣ ባለሥልጣናት ጥንቃቄ ማድረግን መርጠዋል" ሲሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማሪያም ማስታወቃቸውን ደግሞ ሮይተርስ ዘግቧል። ከአንዳንድ ሥፍራዎች ሰዎች መውጣት መጀመራቸውንና በትንበያው መሠረት ሰዎችን ሥርዐት ባለው መንገድ እንደሚያስወጡም ኮሚሽነሩ ጨምረው አስታውቀዋል።

አካባቢው ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልበት ቆይቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG