አዲስ አበባ —
የኤል-ኒኞ ወቅት አብቅቷል የክረምቱ ዝናብም ቀጥሏል።ያለፈው አመት በዚህ ሰዓት ግን ሁኔታው እንዲህ አልነበረም።ወቅቱን ጠብቀው ለሥራ ለተገኙት የዚች አገር አርሶ አደሮች ያሰቡት ዝናብ አልመጣም የለመዱት ሁኔታም አልቀጠለም። 10.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዚጎች የእርዳታ ጥገና ሆነው ቆይተዋል። እንሆ ዘንድሮ ግን ዝናብ እየበዛ ነው። በልግ አብቃይ በሆኑ አከባቢዎች ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ዝናብ ዘንቧል ጎርፍም አስከትሏል።መህር አብቃይ ለሚባሉት ደግሞ እንሆ ክረምቱ ዝናብ የያዘ ይመስላል።
በድርቁ ምክንያት የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ወገኖች ግን እንዲህ በአንድ ጊዜ ከተረጂነት ሊወጡ ኣይችሉም የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ለአሜሪካ ድምፅ እንዳብራሩት ድርቁ ቢያበቃም ተፅዕኖው በተለይም ምርት እስከሚሰበሰብ ይቀጥላል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።