በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በድርቁ ሳቢያ በወላጆቻቸው ያለ ዕድሜያቸው የሚዳሩ የልጆች ቁጥር እየበዛ ነው


በኢትዮጵያ በድርቁ ሳቢያ በወላጆቻቸው ያለ ዕድሜያቸው የሚዳሩ የልጆች ቊጥር እየበዛ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:43 0:00

በኢትዮጵያ በድርቁ ሳቢያ በወላጆቻቸው ያለ ዕድሜያቸው የሚዳሩ የልጆች ቊጥር እየበዛ ነው

“በኢትዮጵያ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋው ባለው ድርቅ ተስፋ የቆረጡ ወላጆች ህጻናት ልጆቻቸውን እየዳሩ ነው” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በዚህ ዓመት ያለ እድሚያቸው የተዳሩ ልጆች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩንም አስታውቋል፡፡ ይህን እድገት ለመቀልበስና ህጻናት ልጃገረዶችን ለመጠበቅ፣ የረድኤት ድርጅቶች፣ በድርቅ ለተጠቁ ቤተሰቦች፣ በጣም የሚያስፈልጋቸውን ውሃና ሌሎች እርዳታዎችን ለማግኘት እየጣሩ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፣ ራሳቸውንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ ያልቻሉ ሰዎች እርዳታ ፍለጋ ወደ ተፈናቃይ ካምፖች እየፈለሱ ነው፡፡ ራሳቸውን በገቢ ደግፈው ለማቆየትም ማናቸውንም ነገር ያደርጋሉ፡፡

ናስቴሆ በኻር አብዲ ያገባቸው በ14 ዓመቷ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የቀደመው ባሏ እሷንና ሁለት ልጆችዋን መደገፍ ስላልቻለ በዚህ ዓመት ደግሞ ሌላ ሰው አግብታለች፡፡

ተፈናቃይዋ ሙሽሪት ናስቴሆ እንዲህ ትላለች፣

"ምን ማድረግ እችላለሁ? እንዳልሰራ ምንም ሙያ የለኝም፣ በዚያ ላይ አልተማርኩም፣ ልጆቼ እየተሰቃዩ ነው፡፡"

18 ዓመት ያልሞላቸው ልጃገረዶች ጋብቻ በባህልም ሆነ በአገሪቱ የተለመደ ነው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት 40 ከመቶ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ሴቶች የተዳሩት 18 ዓመት ሳይሆናቸው መሆኑን ይገልጻል፡፡ ድርቁ ባስከተለው የመተዳደሪያ እጦት ግፊት፣ ያደረባቸው ወላጆች፣ ልጆቻቸውን መዳሩ፣ የአንድ ተመጋቢ አፍ ቀንሶ፣ የጥሎሽም ገቢ ስለሚያስገኝላቸው እንደ እፎይታ ይወስዱታል፡፡

በተባበሩት መንግሥታስት የህጻናት መርጃ ድርጅት፣ የሶማሌ ክልል የመስክ አገልግሎት ኃላፊ ኡትፓል ሞይትራ እንዲህ ይላሉ

"ድርቁ እጅግ በጣም ባጠቃቸው አካባቢዎች፣ በወረዳዎቹ አደጋው የከፋ መሆኑን ይነገረናል፡፡ 63 ከመቶ ያህል ጨምሮ እናየው ነበር፡፡ በእርግጥ ይህ አሃዝ ትክክለኛ ላይሆን ይችላል፡፡ ከተለያዩ ወረዳዎች ማህበረሰቡን በማነጋገር ያገኘነው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ቁጥር በራሱ ህጻናቱ ስላሉበት ሁኔታ የሚገልጸው አስፈሪ ገጽታ አለው፡፡"

ዩኒሴፍ፣ በክልሉ፣ የልጆች ያለ እድሜ ጋብቻ፣ በእጥፍ መጨመሩን ይገልጻል፡፡ ይሁን እንጂ፣ ችግሩ ከዚያም በላይ ሊሆን እንደሚችልም ያሳስባል፡፡

ወላጆች ጉዳዩን በይፋ አይነጋገሩበትም፡፡ ጋብቻዎቹም በይፋ አይመዘገቡብም፡፡ ምክን ያቱም በኢትዮጵያ ህግ ትክክለኛው የጋብቻ ዕድሜ 18 ነው፡፡ ተሟጓቾች፣ ያለ እድሜ ጋብቻ በልጃገረዶቹ ላይ የሚያስከትለውን ችግር ማስተማር ምናልባት ልምዱን ሊቀንስ ይችላል ይላሉ፡፡

አሁንም በዩኒሴፍ የሶማሊያ ክልል የመስክ አገልግሎት ኃላፊ ኡትፓል ሞይትራ እንዲህ ይላሉ

“ራሳቸው ልጆች የሆኑት ወላጆች” በምን ሁኔታ እንዳሉ እያየን ነው፡፡ ያልተመጣጠነ ምግብ ችግር ከፍተኛ ሆኖ ፣ ራሳቸው ልጆቹ ብቻ ሳይሆኑ እነሱ የሚወልዷቸው ልጆች ራሳቸው ከከፍተኛ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ በሽታ ሲጠቁ እንመለከታለን፡፡

ልጆችን በትምህር ቤት ክፍል ውስጥ ማቆየት ካለ እድሜ ጋብቻና ከእርግዝና በመከላከል ይረዳቸዋል፡፡

ከህጻናትን እንዳድን ድርጅት አሊኑር መሀመድ እንዲህ ይላሉ

እንደምታውቁ ትምህርት የለጋ እድሜ ጋብቻን ለመዋጋት ቁልፍ ነገር ነው፤ ልጆችን በትምህርት ቤት ይዞ ማቆየት ጠቃሚ መሆኑን ለወላጆች እንነግራቸዋለን፡፡ ልጆቻቸሁን በመዳር የሚገኝ የአጭር ጊዜ ጥቅም ሳይሆን በረጀም ጊዜ በሚጠቅማቸው ትምህርት ላይ ማዋል አለባችሁ እንላቸዋለን፡፡

ናስቴሆ አብዲ ትምህርት ቤት ከመሄድ ይልቅ የተማረችው ከብቶችን ማሳዳግ ነው፡፡ ያ ችሎታዋ እሷንና እንደሷ የመሰሉ በድርቁ የተጎዱ ሌሎች ሰዎችን አልጠቀመም፡፡ ይሁን እንጂ ለሴት ልጆችዋ የምትመኘው ከሷ የተለየ ነገር ነው፡፡

ተፈናቃይዋ ሙሽራ ናስቴሆ አብዲ እንዲህ ትላለች

"ልጆቼን ለማስተማር አቅጃለሁ እድሚያቸው ሲደርስ ወደ ትምህር ቤት ወስዳቸዋለሁ፡፡ አላህ አቅምና ጤንነቱን ከሰጠኝ አስተምራቸዋለሁ፡፡" ናስቴሆ አብዲ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሌሎች ልጃገረዶች፣ ከጋብቻ ይልቅ ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ የምታበረታታ መሆኑንም ገልጻለች፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ::

XS
SM
MD
LG