በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው ድሪምላይነር የሂትሮው አጋጣሚ


ድሪምላይነር ቦይንግ 787 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ሂትሮው
ድሪምላይነር ቦይንግ 787 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ሂትሮው

ተሣፋሪ ባልነበረበት አይሮፕላን ላይ ዛሬ የተነሣ እሳት የለንደኑ ሂትሮው አይሮፕላን ማረፍያ እንዲዘጋ አድርጓል።





አቶ ተወልደ ገብረማርያም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ
አቶ ተወልደ ገብረማርያም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ተሣፋሪ ባልነበረበት አይሮፕላን ላይ ዛሬ የተነሣ እሳት የለንደኑ ሂትሮው አይሮፕላን ማረፍያ እንዲዘጋ አድርጓል።

እሳቱ የተነሳው ድሪምላይነር ቦይንግ 787 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ውስጥ ሲሆን ተሣፋሪዎች እንዳልነበሩበት ታውቋል።

በአይሮፕላኑ ላይ ጢስ በታየበት ጊዜ ሞተሩ እየሠራ እንዳልነበረና ለስምንት ሰዓታት ያህል እዚያው ቆሞ እንደነበረ እንዲሁም ለምሽት በረራ የተዘጋጀ እንደነበረ ለቪኦኤ የገለፁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የአጋጣሚው መንስዔ ምን እንደሆነ እንደማይታወቅ አመልክተዋል፡፡

በቦታው የእሳት አደጋ መኪኖችና ሠራተኞች ደርሰው አይሮፕላኑን በእሳት መከላከያ አረፋ የረጩት ሲሆን ከተወሰነ ጊዜ አገልሎት ማቋረጥ በኋላ አይሮፕላን ጣቢያው ሥራውን እንደገና ጀምሯል፡፡

ቦይንግ ድሪምላይነር አይሮፕላኖች በባትሪያቸው ችግር ምክንያት በያዝነው ዓመት ቀደም ሲል እንዳይበሩ ታግደው ነበር።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ሚያዝያ ድሪምላይነር አይሮፕላኖችን በረራ ላይ በማዋል የመጀመርያው ሆኖ ነበር።

አይሮፕላኑ ላይ እሳት በታየበት ጊዜ ቆሞ እንደነበረና ተሣፊሪዎችም እንዳልነበሩበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ ኃላፊዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የሂትሮው አየር ጣቢያ ቃል አቀባይ ለቪኦኤ እንደገለፁት የአየር ማረፊያው ከ1 ሰዓት በላይ የተዘጋ ሲሆን፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች እሳቱን መረባረባቸውን ተናግረዋል፡፡

የሂትሮው ኃላፊዎች ለቪኦኤ በሰጡት ቃል አይሮፕላኑ ከተሣፋሪዎች ርቆ በሚገኝ ተርሚናል ላይ ቆሞ እንቅስቃሴ ሳያደርግ መዋሉን አመልክተዋል፡፡
XS
SM
MD
LG