በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ጂቡቲ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ተስማሙ


ኢትዮጵያና ጂቡቲ በጋራ የሚያገናኛቸውን የ767 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ የቧንቧ መስመር ለመዘርጋት ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱ ዛሬ አዲአ አበባ ላይ የፈረሙት፣ የኢትዮጵያ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ዶ/ር ሣሙኤል ሁርካቶ እና የጂቡቲ የተፈጥሮ ኃይል ማመንጫ ሚኒስትር ዮኒስ ጉዲ ናቸው።

ከተከታታይ ሰፊ ውይይት በኋላ ለፊርማ የበቃው ይህህ ሥምምነት፣ የሁለቱንም ሀገሮች ጥቅም ያካተተ ነው ብለዋል የኢትዮጵያው ሚኒስትር።

የጂቡቲው ሚኒስትር በበኩላቸው፣ ሥምምነቱ ረዥም ዕድሜ ያለውን የሁለቱን ሀገሮች ወዳጅነት ያጠብቀዋል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG