በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ጥናት ያደረገ፣ ግሎባል ሲስተምስ ፎር ሞባይል ኮሚኒኬሽንስ አሶስየሽን ወይም በምህፃሩ ጂኤስኤምኤ የተባለ ተቋም፣ 76 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚ እንዳልሆነ አስታወቀ፡፡
ተቋሙ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ፣ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የዲጂታል አገልግሎት ለማግኘት፣ የስማርት ስልክ ቀፎዎች እጥረት አንዱ ችግር መሆኑን አመልክቷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የዘርፉ ባለሞያ ደግሞ፣ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎቹ፣ ትኩረታቸውን በከተሞች ላይ ስለሚያደርጉ፣ በገጠር አካባቢ ይህ ችግር ሊፈጠር እንደሚችል ገልፀዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው በገጠር አካባቢዎች ያለውን የዲጂታል አገልግሎት ለማሻሻል፣ በዚህ ዓመት 250 ሺህ ስማርት የሞባይል ቀፎዎችን የማሰራጨት ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል፡፡
መድረክ / ፎረም