በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ
ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

“በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደ ያለው ጥቃት ይቁም። ግድያዎቹ በገለልተኛ ወገን ይጣሩ።” ኢትዮጵያውያኑ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና ምክር ቤቶች ያስገቡት ደብዳቤ።

ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ያካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:45 0:00

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።

“በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደ ያለው ጥቃት ይቁም። ግድያዎቹ በገለልተኛወገን ይጣሩ።” የሚሉ እና ሌሎች በርካታ ጥሪዎች የጠየቁበትን ደብዳቤ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያስገቡት ሰልፈኞች፤ በመቀጠልም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የተነጣጠሩ ሁለት የሕግ ረቂቆች ወደ ቀረቡባቸው የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች አቅንተዋል።

“በራሱ የማይተማመን አስተዳደር አገር በሽብር ይመራል! አምባገነንነትን መደገፍ ይቁም!” የሚሉና ሌሎች ልዩ ልዩ የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰማ ነው፤ ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተነሳው ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ፖሊስና ሥርዓት አስከባሪዎች እንደታጀበ፤ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ያቀናው።

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች ከቀረቡት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ካተኮሩት ረቂቅ ሕጎች አንዱ ነገ ይጸድቅ ይሆናል የሚል ተስፋ ከሰልፎኞቱ ዘንድ አሳድሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG